FICHCHE AND UNIQUE CALANDAR SYSTEM OF SIDAMA @UNESCO

GADA SYSTEM NEXT TO CHAMBALALA@UNESCO

gudumalepost.wordpress.com

Fichee “ፍቼ” “ፍቼ” በሲዳማ ባህል ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየ የዘመን መለወጫ በዓል ስሆን ሰፋ ያለ ባህላዊና ማህበራዊ ትርጉም ያለዉ ነዉ :: የፍቼ በዓል የራሱ ታርካዊ አመጣጥ ፣ የአከባበር ዝግጅት፣ የአከባበር ሥነ-ሥርዓት ፣ አብረዉት የተቆራኙ ባህላዊ እሴቶችና እምነቶች እንድሁም ጫዎታዎች ያሉት ነዉ :: በዓሉ ከሁለት ሳምንት ላላነሰ ጊዜ በድምቀት የሚከበር ሲሆን አከባበሩም ቅደም ተከተላዊ ሂደትና በደረጃ እየሰፋ የሚሄድ የጋራ የአከባበር አድምታ ያለው ነው ፡፡ ስለሆነም ፍቼ በቤተሰብ ወይም በጎረቤት ደረጃ ተሰባስቦ በማክበር የሚያበቃ ሳይሆን ከዚህም በሰፋ መልኩ በባህላዊ አደባባይ / ጉዱማሌ/ በጋራ በድምቀት የማክበር ሂደትን ያካትታል፡፡ ለአከባበሩ እያንዳንዱ ቤተሰብ በቅድሚያ እንደ አቅሙ ቅድመ ዝግጅት ያደርጋል፡፡ ከዚሁ አንጻር የቤቱ እመቤት ለበአሉ ቅቤ ታጠራቅማለች ወተት በታጠነ ማለፊያ “ቁሹና” /የወተት እቃ/ ታከማቻለች የእንሰት ውጤት የሆነውን ቆጮ ለበዓሉ በሚሆን መጠንና ጥራት ከወዲሁ ታሰናዳለች፡፡ አባወራው በፍቼ ማግስት / በጫምበላላ/ እለት ለከብቱ የሚያበላውን ቦሌ ያዘጋጃል፡፡ ልጃገረዶች ለበአሉ መዋቢያ ለእግሮቻቸውና ለእጆቻቸው ጣቶች ቀለበት፣ ለፀጉራቸው መስሪያ “ሄቆ” /የተለያዩ ቀለማት ያሉት የቱባ ክር/፣ ጨሌ፣ ለአንገታቸው ቡሪቻና ዶቃ የጌጥ አይነት ለጸጉራቸው…

View original post 452 more words

Leave a comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.